ሀገር አቀፍ የፆምና የፀሎት ምህላ አዋጅ

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱን አመት በሰላም ለመቀበል ያለመ ለ5 ቀናት የፀሎት መርሐግብር አወጀ።

የፀሎት መርሐግብሩ ከጷግሜ 1 እሰከ 5 የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባኤው አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የሰላም ጥሪን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

አገሪቱ ያጋጠማት ወቅታዊ ችግር በይቅርታና በፍቅር እንዲፈታ የተለያዩ እምነት የሚከተሉ ዜጎች በየሐይማኖታቸው የልዩ ፀሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል።

በሁለቱም ወገኖች ያሉና በትግል ውስጥ ያሉ አካላት ለእርቅ ዝግጁ ሆነው አገሪቷን ማሻገር ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ኢትዮጵያ አሁን ወዳለችበት ጦርነት እንዳትገባ ምዕመናንን ስለሰላም ከማስተማር ባለፈ ፖለቲከኞች ህዝቡን ወደ ጦርነት እንዳያስገቡ ሲሸመግል መቆየቱንም አስታውሷል።

አሁንም ምዕመናን እና የፖለቲካ አመራሮች ለሰላም መቼም ቢሆን ረፍዶ አያውቅም እና ሁሉም ወገን ወደ ሰላም እንዲመለሱ አሳስቧል።

የሀይማኖት አባቶችም ምዕመናኑን ስለ ሰላም ማስተማራቸውን እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው ፥ በጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ንጹሀንን፣ የማምለኪያ ስፍራዎችን በጦርነቱ እንዳይጎዱ አዲያደርጉ ብሏል ፤ “ያለንበት ጦርነት ወደ አዲሱ 2014 ዓመት እንዳይተላለፍ ሁላችንም የሚጠበቅብንን እናድርግ” ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post