ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ።

ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣ የጃንሜዳና ልሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት ቋሚ ሲኖዶስ በሚያስቀምጠው አቅጣጫና ጊዜ ቀጠሮ መሰረት በተለዋጭ ቀጠሮ የሚካሔድ ይሆናል ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚቀጥለው ቀጠሮ ጀምሮ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ዛሬ የመስቀል አደባባይን አስመልክቶ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ እንደነበር አስታውሷል።

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀጠሮ በተያዘበት ቦታና ሰአት የተገኙ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት ዛሬ በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ የዛሬው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀርቷል ብሏል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ለመወያየት እና አብሮ ለመስራት በማንኛውም ሁኔታና ሰአት ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

ከላይ ያሉት መረጃዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኙ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ለምን እንደቀረ የተሰጠ ግልፅ ማብራሪያ ማግኘት አልቻልንም።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post