በበቆሎ ውስጥ ተደብቆ ሊዘዋወር የነበረ ከ800 በላይ ጥይት ተያዘ !

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ800 በላይ ጥይቶችን በበቆሎ ውስጥ ደብቆ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ግለሰቡ ወንጀሉን የፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አውቶቡስ ተራ ትንሿ መናኸሪያ ግቢ ነው፡፡

በሁለት ከረጢት በያዘው በቆሎ ውስጥ 200 የብሬን እና 668 የክላሽ ንኮቭ በአጠቃላይ 868 ጥይቶችን ቀላቅሎ በመደበቅ በተሽከርካሪ ጭኖ ለማዘዋወር ሲንቀሳቀስ በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ የመናኸሪያው የስነ-ስርዓት ተቆጣጣሪዎች ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ተገልጿል።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post