በ ” FIAS 777 ” በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት አጭበረበሩን ካሉት መካከል እጅግ በጣም በጥቂቱ ፦

📩 ” 40000 ብር ተበልቻለሁ ”

📩 ” በFIAS እኔም 30 ሺህ ብር ተብልቻለሁ ”

📩 ” እኔም ገንዘቤን ተበልቻለሁ ፤ ተበድሬ ነበር የገባሁት በሰዎች ጉትጎታ ኤጀንቶቹም አድራሻቸውን አጥፍተዋል ”

📩 ” በFIAS 777 የተዘረፉ በሚያውቋቸው ኤጀንቶች ላይ ክስ ለመስረት እያተዘጋጁ ነው ”

📩 ” ዘንድሮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ የምመረቅ ዘንድሮ ነበር ነገርግን ከቤተሰብ ለመመረቂያ ልብስ ብር አስልኬ fias777 ለተባለ አጭበርባሪ platform ልኬ ምንም ብር ሳይገባልኝ በሉት። ከተቻለ እርምጃ እንዲወሰድበት አሳስባለሁ። በተጨማሪ ሌሎች የማጭበርበሪያ መንገዶችን ለምሳሌ ፦ HDU, DH አና የመሳሰሉ platform እየተጠቀሙ ስለሆነ ማንም እንዳይጭበረበር ”

📩 ” የመንግስት ያለህ እኛ የFIAS ተጠቃሚወች ድርጅቱ ሀገረ መንግስቱ እውቅና የሰጠው ነው ተብለን ነው የገባንበት ሊንኩ ከተዘጋ ጀምሮ ገንዘብ ገቢና ወጭ እሚያደርጉልን ኤጀንቶች ቴሌግራም አካውንታቸውን ድሌት አርገው ከኛ ጋ የተጻጻፋትን አጥፍተው ነው ውሀ ሽታ የሆኑት በመቶ ሽወች የሚቆጠር ገንዘብ vIP Upgrade ያደረጉ ልጆች እያበዱ ነው። ”

📩 ” እዚህ ኢትዮጵያ ሲያስተባብሩ የነበሩት ይታወቃሉ ፤ ልብስ ለብሰው በአደባባይ ሲታዩም ነበር ፤ እንዴት እና ገንዘቡን የት እንዳደረሱት ይጠየቁ ”

📩 ” 30 ሽህ ብር አንድ ብር ሳላወጣ ተበልቻለው ባንክ የከፈልኩበትን ደረሰኝ ማቅረብ እችላለሁ ”

📩 ” በሰው በሰው ገብቼ 30 ሺህ ብር ተበልቻለሁ ፤ ስለድርጅቱ አንዳች ነገር አላውቅም ”

📩 ” እሄ website በ internet ነው እሚሰራው ግባ ብሎ በማላቀዉ ነገር fias 777 lay ኣስገብተዉ አሁን ላይ እስከ100 ሺህ ሚገመት ብር ከሰዉ ኣስበድረው ኣስበልተውኛል:: የ bank full መረጃ አለኝ ”

📩 ” ህጋዊ በመምሰል በጦርነት እና በዚህ በኑሮ ውድነት የሚሠቃየውን ሚስኪኑን ማህበረሰባችንን ዘርፎ ስለጠፋው fias777 ስለሚባል ድርጅት መናገር ፈልጋለሁ። አብዛኛው ሰው ትርፋ አገኛለሁ በሚል መንፈስ ከሰው በመበዴር፣ መሬት በመሸጥ፣ ቋሚ ንብረቶቹን ሳይቀር በመሸጥ ለዚህ ድርጂት መጀመሪያ አካባቢ ከ1000 እስከ 30,000 ብር ገቢ ያዴረጉ ሲሆን አሁን በቅርቡ ሊዘጉት አካባቢ ዴግሞ እስከ 180,000 ብር ድረስ ለዚህ ድርጅት ገንዘባቸውን ገቢ በማድረግ ገንዘባቸው የውሀ ሽታ ሁንዋል ”

(ውድ ቤተሰቦቻችን ፦ ይህ ከብዙ በጥቂቱ ከተላኩት ውስጥ የቀረበ ሲሆን አብዛኛው ሰው በሰው በሰው መግባቱን እና አሁን ስራውን እንሰራለን የሚሉ አካላት መጥፋታቸውን የሚጠቁም ነው ፤ ተበላ የተባለው ገንዘብም እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። የሚመለከተው አካል ገንዘብ ገቢ በተደረገባቸው አካውንቶች መሰረት ሰዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።)

ከዚህ በፊት በኦንላይን በሚሰራ ስራ በርካታ ትርፍ እናስገኛለን እያሉ ስለሚንቀሳቀሱ አከላት ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት መተላለፉ የሚዘነጋ አይደለም ፤ አሁንም በሌላ ስም የሚንቀሳቀሱ አሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post