አሜሪካን በሽምቅ ውጊያ የዘረራት (Ho Chi Minh) ሆ ቺ ሚኒ ማነው?

በኢትዪጵያ የአብዮት ዘመን ይሰሙ ከነበሩ ሞራል ቀስቃሽ ዝማሬዎች መካከል አንደኛው ….

ፋኖ ተሰማራ

ፋኖ ተሰማራ

እንደ ሆ ቺ ሚኒ

እንደ ቼ ጉቬራ ….የሚል ነበር።

 

 

ሆ ቺ ሚኒ ሀገሩ ቬትናምን ከአሜሪካን ወረራ ህዝቡን አስተባብሮ ነጻ ያወጣ ታላቅ ጀግና ነው። እ.አ.አ ሜይ 19 ቀን 1890 ዓ.ም. የተወለደው ሆ ቺ ሚኒ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ፈረንሳይ በኢንዶ-ቻይና ቅኝ ግዛቷ ላይ ታደርግ የነበረውን ጭቆና ይቃወም ነበር። የሆ ቺ ሚኒ የትውልድ ስም Nguyen Sinh Cung ነበር። ሆ ሀገሩን ቬትናምን ከጭቆና ለማውጣት ከጃፓን ፣ከፈረንሳይ እና ከአሜሪካ ጋር ገጥሟል። በተለይም “የቬትናም ጦርነት” በሚባለው ጦርነት ላይ ሆ ቺ ሚኒ ያሳየው ጀግንነት ታሪክ ሲያወሳው የሚኖር ነው።

ሆ ቺ ሚኒ ወደ ትጥቅ ትግሉ ከመምጣቱ በፊት በፈረንሳይ መርከብ ላይ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። በዚህም ስራው ብዙ መጓዝ እና ብዙ ሀገራትን ለማየት ችሏል። በፈረንሳይ የተመሰረተው የፈረንሳይ ኮሚኒስት ፓርቲ አባል የነበረው ሆ ቺ ሚኒ እ.አ.አ በ 1923 ዓ.ም. ሞስኮን በጎበኘበት ወቅት በሌኒን የአብዮት ሃሳብ ልቡ በመነሳሳቱ ወደ ደቡብ ቻይና ተጉዞ በስደት የሚገኙትን የሀገሩን ልጆች በማስተባበር በ1930 ዓ.ም. Indo-Chinese Communist Party (ICP).ን አቋቋመ። ከዛም ወደ ሀገሩ በማቅናት ቬትናምን ከጃፓን ነጻ የማውጣት ትግሉን አቀጣጠለ። ይሄኒ ነው የልደት ስሙ ተቀይሮ የተስፋ እና የብረሃን ቀንዲል መሆኑን የሚገልጸውን “Ho Chi Minh” የሚለውን ስያሜ ከሀገሩ ልጆች ያገኘው።

 

 

በአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ቬትናሞች ነጻ ሀገር መሆናቸውን ቢያውጁም ፈረንሳይ ግን የቬትናምን ነጻ ሀገርነት ለመቀበል ፍቃደኛ አልነበረችም። በዚህም ምክንያት ቬትናሞች ከፈረንሳይ ኃይሎች ጋር ጦርነት ገጥመው ስምንት ዓመታትን ከፈጀ እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ፈረንሳዮች ለሰላም ስምምነት እጃቸውን ዘረጉ። የፈረንሳይ ጉዳይ ቢፈታም ቬትናም ለሁለት ተከፍላ ሆ ቺ ሚኒ የሰሜን ቬትናም ፕሬዝዳንት ሆነ። የሀገሩን አንድነት ለሚናፍቀው የብረሃን ቀንዲ ሆ ግን ሁለት ቬትናም የሚባል ነገር የሚዋጥለት ነገር አልሆነም። በዚህም ምክንያት ኮሚኒስቱ ሆ ቬትናምን አንድ ለማድረግ ታጥቆ በደቡብ ቬትናም ኃይሎች ላይ ጦርነት ከፈተ። ይሄኔ የኮሚኒስት ኃይሎች መስፋፋት ያሰጋኛል ያለችው አሜሪካ ደቡብ ቬትናምን ለመርዳት ጦርነቱ መኻከል ጠልቃ ገባች። ሆ ቺ ሚኒ ግን ለአሜሪካኖቹም ቢሆን የሚበገር አልነበረም። ምንም እንኳን ሆ እ.አ.አ September 2ቀን 1969 ዓ.ም. ቢሞትም ያቀጣጠለው አብዮት ፍሬ አፍርቶ ሀገሩ ቬትናም ጠላቷን አንገት አስደፍታ ነጻነቷን ልትቀዳጅ በቅታለች።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post