አሜሪካ ዳግም ወታደሮቿን በሶማሊያ ልታሰማራ ነው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ወታደሮች እንደገና ወደ ጎረቤታችን ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል።

ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 700 የሚጠጉ ሶማሊያ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ ሁሉም ወታደሮቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያደረጉበትን እርምጃ የሚቀለብስ ነው።

አሁን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ምን ያህል ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንደሚያሰማሩ ባይታወቅም፣ ነገር ግን ወታደሮቹ የልዩ ተልዕኮ ኃይል አባላት እና እዚያው ሶማሊያ ውስጥ የሚሰፍሩ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ ሠራዊት አባላት ዳግም ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰማሩ ከመፍቀዳቸው ባሻገር፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተጠርጣሪ የአልሸባብ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ዕቅድ ማጽደቃቸው ተነግሯል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ አሜሪካ ሠራዊቷን ከአፍጋኒስታን ካስወጣች በኋላ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ የነበረውን የፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻን መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ ሰራዊቷን ወደ ሶማሊያ እንደምታሰማራ የተሰማው ትላንት የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዶ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post