ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ማነው?

 

ሙሉ ስሙ Olusegun Mathew Okikiola Aremu Obasanjo ይባላል። እንደ ፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር ማርች 5 ቀን 1937 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ አቢኩታ በተባለች መንደር ነው የተወለደው። ከቤተሰቦቹ ዘጠኝ ልጆች ኦባሳንጆ አንጋፋው ሲሆን ፣ ከዘጠኙ የልጅነትን ኣድሜ በህይወት መሻገር የቻሉት እሱና አንድ እህቱ ብቻ ነበሩ። በልጅነቱ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተለያየ የህይወት ፈተና ውስጥ አልፎ በሚገባ የተከታተለው ኦባሳንጆ እናቱን እና አባቱን በሞት የተነጠቀው በተከታታይ ዓመት ነበር። እናቱን በ1958 ዓ.ም. ሲያጣ አባቱ ደግሞ በዓመቱ እናቱን ተከትለው ለዘላለሙ አሸለቡ። ኦባሳንጆ በትምህርት ቤት ህይወቱ የቦይ ስካውት አባል ነበር። በዚህ ጊዜ የነበርው የፖለቲካ ተሳትፎ ይህ ነው የሚባል ባይሆንም Mathew የሚለውን ስም የቅኝ ግዛት ተቀጽላ ነው በማለት ከስሙ ላይ እንዲነሳ ማድረጉ ይነገራል። ኦባሳንጆ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀቅ በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚያስገባውን ፈተና ተፈትኖ ቢያልፍም የትምህርቱን ወጪ የሚሸፍንለት ሰው ስላልነበረው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሳይገባ ቀረ። በ1958 ዓ.ም. የናይጄሪያ ጦር ለካዴት መኮንንነት ስልጠና ጥሪ ሲያደርግ ኦባሳንጆ ጥሪውን ተቀብሎ ጦሩን ተቀላቀለ።

ኦባሳንጆ እና ውትድርና

ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በ1958 ዓ.ም. ነበር የናይጄሪያን ጦር የተቀላቀለው። በጊዜው ናይጄሪያ ከቅኝ ግዛት ተላቃ የራሷን ልዑዓላዊ መንግሥት ለማቋቋም ደፋ ቀና እያለች ስለነበር አዳዲስ ናይጄሪያዊ የጦር መኮንኖችን ትፈልግ ነበር። ይህ እድል ኦባሳንጆን በእንግሊዝ ሀገር የውትድርና ሳይንስን እንዲማር መንገድ ጠረገለት።

ኦባሳንጆ ሀገሩ ናይጄሪያ ነጻ ከወጣች በኋላ ሰላም አስከባሪ ሆኑ በ1960 ዓ.ም. ኮንጎ ዘምቷል። በኮንጎ በነበረው ቆይታም ሲቪሎችን እና በኮንጎ የሚኖሩ የቤልጄም ዜጎችን ከነበረው የአመጽ ጥቃት የመከላከል ሚናን ኣንደ አንድ የሰላም አስከባሪ ወታደር መወጣት ችሎ ነበር። በዚህ ጊዜ ኦባሳንጆ በአማጺያኑ እጅ ወድቆ ከመሞት ለጥቂት ነበር ያመለጠው።

ከኮንጎው ዘመቻ በኋላ ኦባሳንጆ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ እንግሊዝ Royal College of Military Engineering ተለካ። በዚህ ጊዜ ኦባሳንጆ በነበረው የትምህርት ትጋት “the best Commonwealth student ever” የሚል ማሞካሻ ተሰጥቶት ነበር።

 

 

የኛይጄሪያ የእርስበርስ ጦርነት

በቢያፍራ ጦርነት ጊዜ ኦባሳንጆ የማሪን ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ነበር። በ1970 ዓ.ም. የቢያፍራ አመጽ እንዲቆም እና የናይጄሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቆም አደረገ። በዚህ ጊዜ ኦባሳንጆ በሚሊተሪ ማዕረግ እያደገ ሄዶ በ1972 ዓ.ም. ብርጋዴር ጀነራል ከዛም በ1976 ዓ.ም. ሌተናል ጀነራል ለመሆን በቃ።

ወደ ሥልጣን ጉዞ

በ1976 ዓ.ም. በኮሎኔል ድምካ ተመርቶ በተደረገ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሞት የተረፈው ኦባሳንጆ ከጀነራል ዳንጁማ ጋር በመተባበር መፈንቅለ መንግሥቱን አከሸፈ። ከዚህ በኋላ ጠቅላይ የጦር ካውንስሉ ባደረገው ውሳኔ መሰረት ኦባሳንጆ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር (head of state) ሆኖ ተመረጠ። በዚህ ጊዜ ኦባሳንጆ ሥልጣኑን ለሲቪል ለማስተላለፍ እና የናይጄሪያን ማህበራዊ እድገት እንዲያንሰራራ ለማድረግ ስልጣኑ ያጓጓው ሰው አልነበረም። እ.አ.አ ኦክቶበር 1 ቀን 1979 ዓ.ም. አዲስ ለተመረጠው የሲቪል ፕሬዝዳንት ሼሁ ሻጋሪ ሥልጣኑን አስረክቦ ከጦሩ እና ከአስተዳደሩ ራሱን አገለለ።

ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ

በሳኒ አባቻ የአስተዳደር ዘመን ኦባሳንጆ የፕሬዝዳንቱን አምባገነናዊ አገዛዝ በመቃወሙ ለእስር ተዳርጎ ነበር። መፍፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረሃል ተብሎ በመጀመሪያ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ ቢወሰንም በኋላ ፍርዱ ወደ 30 ዓመት እስራት እንዲቀል ተደርጎለት ነበር። ሳኒ አባቻ (sani abacha) በ1998 ዓ.ም. በድንገት ሲሞት ኦባሳንጆ ከእስር ተለቆ በthe Peoples’ Democratic Party, PDP ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር ጀመረ። በዚህም ምርጫ ኦባሳንጆ አሸንፎ ሜይ 29 ቀን 1999ዓ.ም. የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅቷል። ኦባሳንጆ በፕሬዝዳንትነት እስከ ሜይ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ናይጄሪያን መምራት ችሏል።

 

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post