” ከቤት ውጣ ብላኛለች ” በሚል ምክንያት ሴት አያቱን የገደለው ተከሳሽ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት በፅኑ እስራት ተቀጣ።

#AddisAbaba

” ከቤት ውጣ ብላኛለች ” በሚል ምክንያት ሴት አያቱን የገደለው ተከሳሽ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት በፅኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሃሴ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቀጠና 5 ወጣት ማዕከል አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የ79 ዓመት ዕድሜ ካላቸው ከአባቱ እናት ጋር ይኖር የነበረ ሲሆን ” ከቤት ውጣ ብላኛለች ” በሚል ምክንያት ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አያቱን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ጭንቅላታቸውን በመዶሻ ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡

የተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post