ክንድ ላይ ስለሚቀበር የወሊድ መከላከያ (ኢምፕላንት) ምን ያውቃሉ?

 

ኢምፕላንት ረዘም ላለ ጊዜ የሚሆን የወሊድ መቆጣጠርያ መንገድ ሲሆን ክብ ፕላስቲክ የክብሪትን መጠን ሚያክል መጠን ያላት ሲሆን በዋነኝነት በማንጠቀመው ክንዳችን ስር የሚቀበር ሲሆን ከ3 አመት እስከ 7 አመት ለሚሆን ጊዜ እርግዝናን ይከላከላል። ምንም ኢስትሮጅን ያለያዘ ሲሆን በወጣበት ጊዜ መጸነስ ይቻላል።

እርግዝናን የሚከላከልበት መንገድ

 • እንቁላል ከኦቫሪ ወቶ እንዳይሄድ ይከላከላል(ዋነኛው መንገድ ነው)
 • እንቁላል ከኦቫሪ አልፎ ከወጣ በኋላ ወደ ማህጸን እንዳይደርስ እንቅስቃሴዉን ይቀንሳል
 • የማህጸን የዉስጠኛዉን ግርግዳ ለጸንሱ ምቹ እንዳይሆን ያደርጋል
 • የማህጸን በር ጋር ያለዉን ፈሳሽ በማወፈር የወንዴው ዘር አልፎ እንዳይገባ ያደርጋል።

ጥቅሞቹ

 • አስተማማኝ ነው
 • ጡት ለሚያጠቡ እናቶች ተስማሚ ነው
 • ባስወጣነው ጊዜ ወዲያው እርግዝና ይከሰታል
 • እያስታወሱ መውሰድ ወይም መወጋት አያስፈልግም

የጎንዮሽ ጉዳቶቹ

 • የወር አበባ መዛባት
 • የአባላዘር በሽታን አይከላከልም
 • እራስ ምታት
 • የጡት ህመም
 • ክብደት መጨመር
 • ድብርት ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት የጎንዮሽ ጉዳቶች ሁሌም የሚከሰቱ ወይም የተለመዱ አይደሉም።

መጠቀም የሌለባቸው ማናቸው

 • ለኢምፕላን አለርጂ የሆኑ
 • የደም መርጋት፤ስትሮክ ያለባቸው
 • የጉበት ህመም ያለባት
 • የታወቀ የጡት ካንሰር ያለባቸው
 • ምክንያቱ ያልታወቀ ከማህጸን የሚወጣ ደም መፍሰስ ካለ

ምንጭ፡ Ethiotena

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post