የሰሜን ሸዋ ዞን ሁኔታ ምን ይመስላል ?

የሰሜን ሸዋ ዞን ሁኔታ ምን ይመስላል ? በሰሜን ሸዋ መሰረታዊ አገልግሎቶችና መንግስታዊ አስተዳደር ስራ እየጀመሩ ይገኛሉ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በ5 ወረዳዎች እና በ86 ቀበሌዎች ውስጥ ገብተው የነበሩት የህወሓት ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን ገልፀዋል። ዋና አስተዳዳሪው አቶ ታደሰ ፥ አመራሮች ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና ስራ እንዲያስጀምሩ ፣ የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችም እንዲሟሉ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

” በሁሉም ወረዳዎች የፖለቲካ አመራሩ እና የፀጥታው መዋቅር ወደ ቦታው ገብቷል፤ ስራም እንዲጀምር ተደርጓል፤ ይሄን በጣም በፍጥነት ነው ለመስራት ጥረት ያደረግነው ” ሲሉ ገልፀዋል። የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር አቅጣጫ መቀመጡን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው በአነስተኛ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የጀመረበት ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ትላንት አብዛኛው የመንግስት ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከትላንት አንስቶ ቢሮዎች ተከፍተው ሰራተኞችም ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ ስራ ቦታቸው እየገቡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለመቆጣጠር በቅንጅት እየተሠራ ነው - የዞኑ ፖሊስ መምሪያ -

በሌላ በኩል የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች የተጓደሉ መሰረተ ልማቶች ማለትም የመብራት ፣ ኔትዎርክ ፣ ውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው በሸዋሮቢት፣ ደብረሲና ፣ መሀል ሜዳ ፣ ዘመሮ፣ ሞላሌ አገልግሎቶቹ እንዲመለሱ ተደርገዋል ብለዋል። ” የመብራት አገልግሎት በሸዋሮቢት ፣ ደብረሲና ፣ መሀልሜዳ ፣ ዘመሮ ፣ ሞላሌ ያለ ሲሆን የቀረው መዘዞ ላይ ሲሆን በመዘዞም እንዲጀመር እየተሰራ ነው ፤ የኔትዎርክ አገልግሎት በተመሳሳይ አለ ” ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post