የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን ግድያ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ሰጥቷል።

ሰኞ ዕለት ህይወቷ ያለፈው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተጠረጠረ ተማሪ ትላንት ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት የሰጡ የተጠርጣሪው #ሁለት_ጓደኞቹ የሚከተለውን ብለዋል :-

“ተማሪ ፅጌሬዳ ከተጠርጣሪ ወንጀለኛው ጋር ግንኙነት የነበራት ሲሆን በመሀል ውጪ የነበረ ጓደኛዋ ስለመጣ ግንኙነቱን ማቋረጥ እንደምትፈልግ ገልጻለታለች። በዚህም ተጠርጣሪው ደስተኛ እንዳልነበረና ዛቻና ማስፈራሪያ በጓደኞቿ በኩል ይልክላት ነበር።”

ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ከሁለቱ ጓደኞቹ በአንደኛው ስልክ በመደወል ወደ አስተዳደር ህንጻ አካባቢ እንድትመጣ አድርጓል። በወቅቱ ስልክ ደዋዩና ሌላኛው ጓደኛው አብረውት ነበሩ። “ጉዳያችንን እኛ እንጨርሳለን እናንተ ሂዱ” ብሏቸው ብዙም ሳይቆይ በስለት እንደወጋት ጓደኞቹ ምስክርነት ሰጥተዋል። ሟች ልቤን ብላ ስትጮህ በቅርብ ርቀት የነበሩ የግቢው ጥበቃ አባላት ደርሰው ለማምለጥ የሞከረውን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለውታል።

ተጠርጣሪው በሕግ ጥላ ስር ውሎ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሲሆን ፍ/ቤት ቀጣይ ቀጠሮ እንደሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። የሟቿ አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቿ ወደሚገኙበት ወልቃይት ወረዳ አድ ረመጽ ከተማ መላኩንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በ20 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ተማሪ ፅጌሬዳ በዩኒቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post