የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጉባኤው በስኬት መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ ” የዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲደረግ የአባል ሀገራት መሪዎች መወሰናቸውን ተከትሎ ወንድማዊ አጋርነት የታየበት የኅብረቱ ጉባኤ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል ” ብለዋን።
የኅብረቱ ጉባኤ ፍሬያማ ውይይት የተካሄደበት፣ ለአህጉሪቱ የሚጠቅሙ ውሳኔዎች የተላለፉበት፣ ከምንም በላይ ወንድማዊ አጋርነት የታየበት ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቀ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።