የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ቀብር እና የሚከናወኑ ሥነ ሥርዓቶች

የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ሕልፈተ ሕይወት በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ ረዥሙ የንግሥስና ዘመን እንዲያበቃ አድርጓል።

ንግሥቲቱ ሐሙስ ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም. በቤተሰብ አባሎቻቸው ተከብበው ስኮትላንድ በሚገኘው ባልሞር ቤተ-መንግሥት ውስጥ ነበር በሰላም ያረፉት።

የአገሪቱ ዜጎች ለንግሥቲቱ ያላቸውን ክብር እየገለጹ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናት ቀብራቸውን በተመለከተ ሊኖሩ የሚችሉት ሥነ ሥርዓቶች የሚከተሉት ናቸው።

አስክሬናቸው ከስኮትላንድ ወደ ለንደን ከመጣ በኋላ ቀድሞ የሚያርፈው በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ነው።

የንግሥቲቱ እናት በሞቱ ጊዜ አስከሬናቸውን ለመሰናበት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሰዓታት ተሰልፈው ጠብቀዋል

አስክሬኑ ከይፋዊ መኖሪያ ቤታቸው ዝግ ባለ ፍጥነት በቤተሰብ አባላት እና በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ ወደ ዌስትሚንስተር አዳራሽ ያቀናል።

ሥርዓተ ቀብር ከመፈጸሙ በፊት ለአራት ቀናት በዌስትሚኒስቴር አዳራሽ ያርፋል።

በእነዚህ ቀናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስክሬኑን በክብር ይሰናበታሉ።

ከብሪታኒያ መንግሥት መቀመጫ አካባቢ የሚገኘው ዌስትሚኒስተር ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚገኘው አዳራሽ ከህንጻው ጥንታዊ ክፍሎች አንዱ ነው።

ከዚህ ቀደም እአአ 2002 በዚህ ስፍራ ቀብራቸው የተፈጸመው የኤልዛቤጥ እናት ነበሩ። የኤልዛቤጥ እናት አስክሬንን ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ በአካል ተገኝተው ተሰናብተዋል።

የንግሥቲቱ የሬሳ ሳጥን

የአስክሬን ሳጥን ዘውዱን እና ዩናይትድ ኪንግደምን በሚወክለው ‘ሮያል ስታንዳርድ’ ሰንደቅ አላማ ይሸፈናል። አስክሬኑ ዌስትሚኒስቴር አዳራሽ ከደረሰ በኋላ ደግሞ ዝውዱ የአስክሬን ሳጥን ላይ ይቀመጣል።

የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዌስትሚንስትር አቤይ ከሁለት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የሚፈጸምበት ቀንን የባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ያስታውቃል።

ዌስትሚኒስቴር አቤይ

አቤይ በብሪታኒያ ነገስታት ታሪክ ውስጥ በርካታ ታሪክዊ ክስተቶችን ያስተናገደ ቤተ መቅደስ ነው። እአአ 1953 ላይ የኤልዛቤጥ የንግሥና ሥነ ሥርዓታቸው የተከናወነ ሲሆን፣ የሠርግ ሥነ ሥርዓታቸውም የተፈጸመው በዚሁ ቤተ መቅደስ ነው።

ዌስትሚኒስቴር አቤይ

ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በአቤይ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሳይካሄድ ቆይቶ የኤልዛቤጥ እናት የቀብር ሥነ ሥርዓት እአአ 2002 ተከናውኖበታል።

በዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም የበርካታ አገራት መሪዎች ወደ ለንደን ተጉዘው ከንጉሣውያን ቤተሰብ ጎን ይቆማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሽኝት መስመር

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዕለት አስክሬኑን ከዌስትሚኒስተር አዳራሽ ወደ ዌስትሚኒስቴር አቤይ በሰረገላ ማጓጓዝ ይጀምራል።

ከአስክሬኑ ጀርባ ንጉሥ ቻርልስ ሦስተኛን ጨምሮ በርካታ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ይከተላሉ።

ሥነ ሥርዓቱን የሚመሩት የዌስትሚኒስትር ካህን ዴቪድ ሆይል ከካንትበሪው አርክቢሾፕ ጀስቲን ዌብሊ ጋር በመሆን ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ጥቅስ እንዲያነቡ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን

 

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሚፈጸምበት ዕለት ከሰዓት በኋላ የንግሥቲቱን አስክሬን የያዘው የሬሳ ሳጥን በዊንዘር ቤተ መንግሥት ውስጥ ወደሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-መቅደስ ያቀናል።

የአስክሬን ሳጥኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው የንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ መታሰቢያ ቤተ መቅደስ ይገባል።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post