የጦርነት ካሳ (War Indemnity) ታሪኮች

 

በሁለት ወገን መካከል የተደረገ ጦርነት በአንድ ወገን አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ በጦርነቱ ለደረሰው ቁሳዊ እና ማህበራዊ ኪሳራ  አንድን አካል ካሳ መጠየቅ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ታሪክ ነው። ለምሳሌ ሮም ከአንደኛው እና ከሁለተኛው የፑኒክ ጦርነት(punic war) መጠናቀቅ በኋላ በካርቴጅ ላይ ከባድ የጦር ካሳ ክፍያን(indemnities) ጥላ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በድህረ ፍራንኮ-ፕሩሲያ እና በመጀመሪያው ሲኖ-ጃፓን (First Sino-Japanese War) ጦርነት ተመሳሳይ የጦር ካሳ ክፍያዎች መፈጸማቸውን ታሪክ ይነግረናል።

በዋተርሉ ጦርነት የታላቁ ናፖሊዮንን ሽንፈት ተከትሎ ፈረንሳይ 700ሚሊዮን ፍራንክ የጦርነት ካሳ እንድትከፍል ተፈርዶባት ነበር። ይህ የጦርነት ካሳ በታሪክ በጦርነት የተሸነፈች ሀገር የከፈለችው ውዱ ካሳ ተደርጎ ይነሳል። እ.አ.አ በ1897 ዓ.ም. ግሪክ ከቱርክ ጋር ያደረገችው ጦርነት ካበቃ በኋላ ለቱርክ ወደ አራት ሚሊዮን ዩሮ እንድትክስ ተጠይቃ ነበር። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ማግስት ደግሞ ሩሲያ፣ቡልጋሪያ እና ጀርመን ይህን መሰሉን የጦርነት ካሳ ለመክፈል የተገደዱ ሀገራት ነበሩ። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ ከJuly 17 and August 2, 1945, በተደረገው የPotsdam conference የ23 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የጦርነት ካሳ እንድትከፍል ተፈርዶባት ነበር።

ታሪክ እንደሚያስረዳን በጀርመን ላይ ተጥሎ የነበረውን የጦርነት ካሳ እዳ በተለይም አሜሪካ በሚገባ ተጠቅማበታለች። አሜሪካ ይህን የካሳ ክፍያ መሰረት በማድረግ ብዙ ማሺነሪዎችን እና የቴክኖሎጂ እውቀቶችን ከጀርመን የወሰደች ሲሆን የፈጠራ መብቶችንም (patent right) ጭምር ከጀርመን እጅ አስኮብልላለች። በቴክኖሎጂ እና በማሽነሪ ከተከፈለው ካሳ ባሻገር የጀርመንን እዳ ለማቅለለ ቁጥራቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ጀርመናዊያን የጦር ምርኮኞች በአሜሪካ ፣አውሮፓና ካናዳ በአስገዳጅ የጉልበት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ተደርገዋል።

ሌላዋ የጦርነት ካሳን የመክፈል ታሪክ ያላት ሀገር ጣሊያን ናት። ጣሊያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ተከትሎ እ.አ.አ በ1947 ዓ.ም. በተደረሰው የሰላም ስምምነት (treaty of peace) ለዩጎዝላቪያ 125 ሚሊዮን ዶላር፣ለግሪክ 105 ሚ.ዶላር፣ ለሩሲያ 100ሚ.ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 25ሚ.ዶላር እንዲሁም ለአልባኒያ 5ሚ.ዶላር ካሳ ለመክፈል ከስምምነት ደርሳ ነበር።

የገልፍ ጦርነት ካሳ (Gulf War reparations)

የገልፍ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ኢራቅ United Nations Security Council Resolution 687ን በመቀበል በኩዌት ላይ ለፈጸመችው ወረራ እና ላደረሰችው ጉዳት በUnited Nations Compensation Commission በኩል ከሶስት መቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ ለመክፈል ተስማምታ ነበር። በዚህም መሰረት እስከ ጁላይ 2019 ባለው ጊዜ ወደ 50 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የሚሆን ገንዘብ ከኢራቅ የነዳጅ ገቢ ድርሻ ተቀናሽ ተደርጎ ለኩዌት ተከፍሏል።

U.N. Defers Iraq's $4.6 billion Gulf War Reparations to Kuwait- Al Manar TV Website Archive

 

የጦር ካሳ (indemnity) በሁለት አይነት መልኩ ሊከፈል ይችላል። አንደኛው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ሁለተኛው መንገድ አንዲት ሀገር ካላት ብሔራዊ ሃብት ላይ ወይም ካላት ገቢ ላይ ለተካሽ ሀገር የምታጋራበት መንገድ ነው። ሁለተኛው አይነት የካሳ ክፍያ መንገድ አንዲት ሀገር ከሀገር ውጪ ያላይን የሃብት ባለቤትነት መብት ለተካሽ ሀገር አሳልፎ መስጠትንም የሚያካትት ነው።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post