የጨው መብዛት የሚያመጣው የጤና ጣጣ!!

የጨው መብዛት የሚያመጣው የጤና ጣጣ!!

!

ጨው 40 በመቶ [40%] ሶዲየም እና 60 በመቶ [60%] ክሎራይድ በውስጡ የያዘ ሲሆን በጣም በትንሹ (trace) ካልሲየም፣ ፖታሽየም፣ ብረትና ዚንክ ሊይዝ ይችላል። በአብዛኛው ጨው አዮዲን ተጨምሮበት ለፍጆታ ይቀርባል። አብዛኛው ምግብ ውስጥ ጨው አለ።

ምንም ነገር በልኩ መጠቀም ትክክል ቢሆንም 90 በመቶ (90%) የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ግን ጨውን ከልክ በላይ ይጠቀማል። በመሆኑም ከታች ለዘረዘርኳቸው በሽታዎች ይጋለጣል።

1. የልብ ድካምና ተያያዥ በሽታዎች

የጨው በደም ውስጥ ከፍ ማለት ውሃ ከሚፈለገው በላይ ወደ ደም ስር በመሳብ የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋል። የደም ግፊት ደሞ በልብ ላይ ጫና በመፍጠር ከጊዜ ወደ ጊዜ ልብን ያደክማል። ማንኛውም ሰው የጨው መጠንን በመቀነስ የሚጠቀም ሲሆን የደም ግፊትና የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች ግን ከአንድ ማንኪያ ወይም ከ6 ግራም በታች እንዲወስዱ ይመከራል።

2. የጨጓራ ካንሰር

በአለማችን በገዳይነት በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጠው የጨጓራ ካንሰር ጨው በብዛት በሚጠቀሙ ሰዎች ይበዛል። ጨው በብዛት የሚጠቀሙ ስዎች በልኩ ከሚጠቀሙ ሰዎች አንዛር ሲታይ በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድላቸው በ 68 በመቶ {68%} ከፍ ይላል። ለዚህ ብዙ ማብራሪያ ቢኖረውም የኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ ማደግና የጨጓራ ግድግዳ መቁሰል በዋንኛነት ይጠቀሳሉ።

3. ስትሮክ (ወደ አንጎል የሚሄድ ደም መቋረጥ ወይም አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ)፣ ይህም ችግር ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ይያያዛል።

4. የደም ግፊትና እሱን ተከትሎ የሚመጣው የጤና እክል። ለሌሎች ያጋሩ! ህይወት ያድኑ!

 


 

 

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post

Daily Feta

Other Post