ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል

በጢጣ በኩል ሰብሮ በመግባት የደሴ ከተማን ለመቆጣጠር የሞከረው አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።የመጣውን ኃይልም ደሴ ከተማ ከመግባቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ባለበት ማስቀረት መቻሉን በወሎ ግንባር ወራሪውን ኃይል እያፀዱ የሚገኙ የመከላከያ እና ደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።የደሴ ከተማ እና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለመ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔ እና ጀግንነት ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በግንባሩ የተሰለፉ የሠራዊት አመራር እና አባላትም ወራሪውን ኃይል ለአንዴ እና መጨረሻ ለማጥፋት አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸሙ እንደሚገኝ አመላክተዋል።በኩታበር በኩል አሰፍስፎ ደሴን ለመውረር የመጣው ወራሪ ኃይልም ምንም ማድረግ እንዳይችል ደርጎ መደቆሱን ገልጸዋል።በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብተው የነበሩ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂዎችም ባሉበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው መሸኘታቸውን ምንጮች ለኢዜአ አረጋግጠዋል።

ደሴ እና አካባቢዋን ለመውረር ከየአቅጣጫው ተሰባስቦ አሰፍስፎ የነበረውን ኃይልም አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የደሴን ከተማ በወገን እጅ እንዳለች ማስቀጠል መቻሉን ገልጸዋል።የደሴ ከተማ እና አካባቢው የሽብር ቡድኑን የአፈሳ ወሬ ባለመስማት አካባቢውን ፀንቶ እንዲጠብቅ እና ለግንባሩ ሠራዊት ሲያደርጉት የነበረውን ደጀንነት እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።

Celebrity News
Daily Feta Posts

Recent post