” ገንዘባችንን ተበላን ” እኚሁ አባላት ገንዘባችን ተበላን ያሉት እራሱን ‘ FIAS 777 ‘ እያለ በሚጠራው ድርጅት ነው

” ገንዘባችንን ተበላን ”

ገንዘባችንን ተበላን ያሉ እጅግ በርካታ ወጣቶች የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መቀበያን @tikvahethiopiaBOT አጨናንቀዋል።

እኚሁ አባላት ገንዘባችን ተበላን ያሉት እራሱን ‘ FIAS 777 ‘ እያለ በሚጠራው ድርጅት ነው።

ይሄ FIAS 777 የሚባለው ” በኮሚሽን የሚሰራ ስራ ” በማለት የበርካቶችን ገንዘብ ሲቀበል ነበር።

ስለዚህ FIAS 777 ከዚህ በፊት የቀረበውን ያንብቡ : t.me/tikvahethmagazine/15060

አሁን ላይ እነዚሁ አካላት የበርካቶችን ገንዝብ ተቀብለው ፦
– አድራሻቸውን ማጥፋታቸው
– የቴሌግራም ገፆቻቸውን እና ዌብሳይታቸውን መዝጋታቸውን
– ኤጀንት የሚባሉትን ማግኘት እንዳልተቻለ ተገልጾልናል።

ይሄ ድርጅት ነኝ የሚለው አካል ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ምዝገባ እንዳካሄደ ገልጾ ነበር ሲያስነግር የነበረው ነገር ግን የተመዘገበበት ማስረጃ የለም።

አሁን ላይ ገንዘባችንን ተበላን ያሉ የቴሌግራም ግሩፕ ከፍተው ቀጣይ ማድረግ ስላለባቸው ሂደት እየተነጋገሩ ሲሆን በቁጥራቸው ከ2000 ይልቃል።

አንድ ሰው ከ3 ሺ ብር አንስቶ እስከ 30 ሺ ብር ድረስ ገቢ ያደረገባቸውን የባንክ ማስረጃዎችን መመልከት ችለናል። አንዳንዶች በዚህ ሂደት ተበድረው ጭምር ነው ገንዘብ ሲልኩ የነበሩት።

እነኚሁ አካላት አንድም በዚህ ተደራጅተው ሲሰሩ የነበሩ አከላት እንዲጠየቁና ሌሎችም በመሰል ድርጊቶች እንዳይጨብረበሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይሄ FIAS 777 የተባለው አድራሻውን ፣ ቢሮው ፣ ኃላፊው ስለማይታወቅ ጉዳዩን ለመከታተልና ለመጠየቅ አልተቻለንም።

ገንዘባቸውን ስለተበሉ አካላት በምን ህግ አግባብ እንደሚታይ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር እንጥራለን።

አሁንም ጥንቃቄ !

Breaking News
Daily Feta Posts

Recent post

Ethiopian Movies

Other Post